25/02/2026
part 3 ✍️✍️ የመጀመሪያዎቹን ገፆች ማንበብ እንዳትረሱ ይሄኛውን ከማንበባቹ በፊት።
✍️✍️ ከቤተክርስቲያን ወደ ቤት ሸኝቶኝ እሱም ወደ ቤቱ እኔም ወደቤት ገባሁ። ገብቼ ልብሴን እየቀየርኩ ሀሳቤን መሰብሰብ አልቻልኩም የቀየርኩትን ልብስ እንደነገሩ ወርውሬ ፍራሼ ላይ አረፍ አልኩ። ስልኬን አነሳሁ ስሙን ከስልኬ ላይ ከመዘገብኩ በኋላ ቴሌግራም ላይ ፎቶውን ለማየት ፈለኩት ፎቶ አላስቀመጠም። ስልኬን በእጄ እንደ ያዝኩ ከራሴ ጋር መጣላት ጀመርኩ። አንቺ ምን ሆነሻል በአንድ ቀን ሁሉም እንዳልነበር የምታደርጊው ጤነኛነሽ እራስሽን ተቆጣጠሪ የታየ ሁሉ አይገኝም የተሰማ ስሜት በሙሉ ልክ ነው ማለት አይደለም ተረጋጊ ለራሴ በቁጣ ተናገርኩ። ተነሺ ህይወትሽን ኑሪ አልኩ። ቁጣውን ልክ እንደሆነ ስለገባኝ ካለሁበት ተነሳሁ ነጠላዬን ማጣጠፍ ጀመርኩ ለብሼው የነበረውን ልብስ በአግባቡ አስቀመጥኩ። ከዚህ ሀሳብ ለመውጣት እራሴን በስራ መጥመድ ፈለኩ ሳስታውስ ነገ ወደ ስራ እገባለሁ ስለዚህ ለምሳዬ የሚሆን ምግብ ማብሰል አለብኝ። ቀጥይ ወደ ስራ ብዬ እራሴን ጀመርኩ። ለምሳ ምን ልያዝዝዝዝዝ ትዝ ሲለኝ ምስር አለ ምስር ወጥ ለመስራት ጉድ ጉድ ለማለት ስጀምር ከስልኬ የመልዕክት ድምፅ ሰማሁ 🙄 በአዕምሮዬ እሱ ስለነበር እያሰብኩ የነበረው ሌላ መልዕክት ባይሆን እየተመኘሁ ወደ ስልኬ አመራሁ ከፈትኩት ቴሌ ነው ደሜ ተንተክትኮ መልዕክቱን አጥፍቼው ወደ ስራ ተመለስኩ። ሽንኩርት እያቁላላሁ ምስሬን ማጠብ ስጀምር በድጋሚ የመልዕክት ድምፅ ሰማሁ። በድጋሚ ቴሌ እንደሚሆን ገምቼ ሰራዬን ቀጠልኩ ግን አዕምሮዬ የስልኩ መልዕክት ላይ ነው። ምስሩን ማጠቡን ጨርሼ ወደ ስልኬ ሳመራ ድጋሚ መልዕክት ገባ። ከፈትኩት እሱ ነበር። "እንዴት አመሸሽ " ,,,,,,,, " እጆቼ እጆችሽ መንካታቸውን ማመን አልቻልኩም ፣ አይኖችሽን በቅርበት ማየት መቻሌን ማመን አቅቶኛል ከዛም አልፎ ከጎንሽ ተራመድኩ" ይላል መልዕክቱ በስመአብ ሰው በእርጅና ዘመኑ እንዲህ ያብዳል? የ33 አመት ሴት ሳይሆን በውስጤ የምትዘለው ሴት የ16_18 ዓመት ያለች የህፃን ልብ ተሰካ በልቤ ውስጥ ልቤ በደስታ ዘለለ ይሄ ሁሉ አመት በትንሹ ደስ ብለውኝ የሚያውቁ ሰዎች እንጂ እንደዚህ አይነት የሰው መውደድ ደርሶብኝ አያውቅም። መልዕክቱን ለረጅም ሰዓት ስመለከት ቆይቼ መልዕክት ለመመለስ ወደ እራሴ ስመለስ ስጎዬ አሯል ይሸታል ወይኔኔኔኔኔኔኔ ምን ጉድ ነኝ እራሴን እየታዘብኩ ምድጃውን አጥፍቼ ድስቱን አወረድኩት አይጠቅምም ደፋሁት አሁን በድጋሚ ሽንኩርት ከትፌ ስጎ መስራት አለብኝ? ኤጭጭጭጭጭ ምን አይነት ነው ተነጫነጭኩ በራሴ። ትዝ ሲለኝ መልስ አልመለስኩለትም ያው ሴትም አይደለው የተሰማኝን ሁሉ በአንዴ መግለፅ አልፈለኩም እና አጠር ያለች መልስ መለስኩ" ስለተዋወቅን ደስ ብሎኛል" ብዬ መለስኩለት። ወይኔ እኔን ያላየ ከዛ ስጎዬን በድጋሚ ሰራሁ ምስሬን ሰርቼ ጨረስኩ ። የሰራሁበትን አጣጥቤ ቤቴን አስተካክዬ ወደ ፍራሼ ሄድኩ። መልዕክት በድጋሚ መጣ " ተኛሽ አበባዬ" የሚል 😥🙄🥰ልቤ ፈሰሰ መለስኩለት" አይ አልተኛሁም" ብዙ ሀሳብ ወደ ጭንቅላቴ መጣ እራሴን ተቆጣጠርኩ ተቆጣሁ ስልኬን ዘጋሁት ሁኔታዬ አያምርም ። የምሽቱን ፀሎት ፀልዬ ወደ እንቅልፍ ሄድኩ ግን መተኛት አልቻልኩም ስልኬን ከፈትኩት መልዕክት ልኳል። እያወራን ለሊቱን አጋመስን ሳስታውስ ነገ ስራ ገቢ ነኝ በቃ ደህና እደር ጠዋት ስለምነሳ መተኛት አለብኝ አልኩት ሀሳቤን ተቀብሎ መልዕክት መላላክ አቆምን እኔ ግን እንቅልፌ ጠፋ። ጣራ ጣራ እያየሁ መልዕክቶቻችንን ደጋግሜ እያነበብኩ ለሊት 9:15 ሆነ ለመተኛት መታገል ጀመርኩ በስንት ትግል እንቅልፍ ወሰደኝ። ጠዋት12:23 ሲል ነቃሁ እንደረፈደ ተማኝ አዲስ ስራ ጀማሪ አይደለሁ? በፍጥነት ከፍራሼ ተነሳሁ ፊቴን ታጠበብኩ የእለቱን ፀሎት አደረስኩ የተኛሁበትን አስተካከልኩ።ምሳዬን መቋጠር ጀመርኩ እሱን ስጨርስ ወደ ልብሴ ሄድኩ መረጥኩ ያው እንደተለመደው ቆንጆ አለባበሴን ለበስኩ ፀጉሬን አስተካክዬ ሽቶዬን አርከፈከፍኩት ፊቴ ላይ ከውሀ ውጭ የምጠቀመው ተጨማሪ ነገር ስለሌለ ቶሎ እጨርሳለሁ። እራሴን በመስታውት እየተመለከትኩ ተመስገን ይሄን ሞገስ ያላሳጣሀኝ ብዬ ሀብታም መሳይ ድሀ ሆኜ ወጣሁ ምሳ እቃዬን ከጃንጥላ ጋር በትንሽ ማንጠልጠያ ይዤ ስልኬን በእጄ አድርጌ በሬን ቆልፌ ወደ ስራ። ስራዬ ካለሁበት ብዙም አይርቅም የአንድ ታክሲ ጉዞ ነው። የውጭውን በር ከፍቼ ወጣሁ ዘግቼው መንገዴን ጀመርኩ ጥቂት እንደ ተራመድኩ መልዕክት ደረሰኝ ስልኬ እጄ ላይ ስለነበር ከፍቼ አየሁት እሱ ነበር "እንዴት አደርሽ የእኔ ፀሀይ" ኦኦኦኦኦኦኦኦ ወዮዮዮዮ አሰብኩ እያየኝ እንደሆነ ስለዚህ ከፊቴም ከአካሌም የተለየ እንቅስቃሴ ማሳየት አልፈለኩም በውስጤ ግን እየዘለልኩ ነው። መልዕክቱን መለስኩ "እንዴት አደርክ" በነገራችን ላይ እንዴት አደርሽ የእኔ ፀሀይ የሚለው መልዕክቱ ለእኔ ከምኔው ሰማይ እንደደረስኩ ባላውቅም እራሴን ከፀሀይ ውስጥ ፈለኩ እላይ ፀሀይ ላይ የተሰካሁ መሰለኝ ልክ እንደ ፀሀይ የማበራ መሰለኝ። ወይ ጉድ የሴት ችግሯ ይሄ ነው በጆሮዋችን ያኔ ሰይጣን ከገነት ለማባረር የተጠቀመው ቃላቶች ዛሬም በጆሮ ማመኑን ተያይዘነዋል ብቻ የማነበው ወደ ጆሮዬ ስለሆነ የሚሄደው እንደዛ ቀኔን በብርሀን ሞላልኝ። ይሄን ሁሉ እያሰብኩ ሁለተኛ መልዕክት ገባ " ወደ ስራ ነሽ"? አዎ ወደ ስራ ነኝ። የት ነህ አልኩት ? እዚው ነኝ መምጣት እችላለሁ? ሰላም ልበልሽ? አቤት ትህትናውውውውው ይሄማ ሰው የራሱን ቤት ለመግባት እራሱ የሚያስፈቅድ ይመስላል። አዎ ትችላለህ። ባይለኝም እኔ ላየው ፈልጌ ነበር ከማለቴ ዞር ስል አጠገቤ ነው። ተገርሜ የቱጋር ነበርክ አልኩት እዚው አካባቢ አለኝ ሆሆሆሆሆ ከሰማይ የወረደ ነው የሚመስለው እኮ። ሰላምታ ተለዋወጥን እና አብረን መራመድ ጀመርን። እውይይይይ ዝነጣው ሲያምር የእውነት ወንድ በቃ ደሞ ጠረኑ ንፁ ደስ ሲል ብቻ በጣም እኔ የምወደው አለባበስ ለብሷል። ደስ የሚል ሽቶውን አርከፍክፏል። ስንራመድ ምንም አናወራም እኔም በየመሀሉ እየሰረቅኩ እያየሁት አስባለሁ እሱም እንደዛው። ታክሲ የሚዝበት ቦታ አደረሰኝ ደህና ዋል ብዬው ወደ ታክሲ ገባሁ።እሱ ወደ ኋላ ተመለሰ እኔም ወደ ስራ ሄድኩ። ታክሲ ውስጥ ቁጭ ብዬ ስለ እሱ ማሰብ ጀመርኩ ወይኔ ለካ ሴት ፍቅር ሲዛት ጭንቅላቷን ታጣለች የሚባለው እውነት ነው። እንዴ በአንድ ቀን እንዴት ፍቅር ያዘሽ? አትበሉ ልባችንን ነፃ እና ክፍት ካደረግነው የምንፈልገውን ካወቅን በደንብ የፍቅር ስሜት መሰማት ይችላል።እና ከዛ አዲሱ ስራ ቦታዬ ደረስኩ አይገርምም ሰው አያስተውለውም እንጂ የሁሉም ነገር ምላሽ በአንድ ቀን ሊሆን ይችላል ወይም እኛህ አባት የመረቁኝ ምርቃት ከፀሎቴ ጋር ተባብረው ወደ እግዚአብሔር ደርሶ ይሆናል። ለስጋዬ ለኑሮዬ አዲስ ስራ ለልቤ ለመንፈሴ አዲስ የፍቅር እንግዳ ተያይዘው በአንድ ቀን ወደ ቤቴ ገቡ። በጣም ደስ ብሎኛል ለእኔ አለም ዘጠኝ ሳትሆን አስራ አምስት ሆናልኛለች። ስራ ቦታ ደረስኩ ቦርሳዬን ከጠረፔዛ አስቀምጬ ቀና ስል አለቃዬን ፊት ለፊቴ አየሁት። ድንጋጤዬ ወደር አልነበረውም ........ 🙄🙄🙄🙄✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
✍️✍️✍️መነን ዳንኤል