ROMEL Electrical Equipment

ROMEL Electrical Equipment ROMEL is well recognized and trustworthy brand of high quality, durable Electrical equipment.

30/09/2026
ጥራትን ቀዳሚ ዓላማው ያደረገው ሮሜል ኤሌክትሪካል አዳዲስና ዘመናዊ ምርቶቹን ይፋ አደረገ ።በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ማምረትና አቅርቦት ዘርፍ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ አስተማማኝ ...
22/09/2026

ጥራትን ቀዳሚ ዓላማው ያደረገው ሮሜል ኤሌክትሪካል አዳዲስና ዘመናዊ ምርቶቹን ይፋ አደረገ ።

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ማምረትና አቅርቦት ዘርፍ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ አስተማማኝ ጥራትንና የገበያ መሪነትን ያረጋገጠው ሮሜል ኤሌክትሪካል (ROMEL Electrical Equipment)፣ ለደንበኞቹ አዳዲስ እና ዘመናዊ ምርቶቹን ማስተዋወቂያ ደማቅ መርሃ-ግብር ዑራኤል በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤቱ አካሄደ።
መርሃ-ግብሩ በዋነኝነት "ጥራት የመጨረሻው መዳረሻችን ሳይሆን የማንደራደርበት መነሻችን ነው" በሚለው የድርጅቱ መርህ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ሮሜል በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የኤሌክትሪክ ብራንድ እንዲሆን የጀርባ አጥንት ለሆኑ የሮሜል ደንበኞቹም ምስጋናን አቅርቧል።
በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሮሜል ኤሌክትሪካል ቺፍ ማርኬቲንግ እና ሺያጭ ኦፊሰር :-
" የሮሜል ደንበኞች የረጅም ዓመት አብሮነት ጉዞ እና የሮሜል አካል በመሆን በሀገራችን ቀዳሚ ብራንድ እንዲሆን ላበረከቱት ጉልህ አስተዋፃ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ። አክለውም ድርጅቱ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ኢቨስትመንት በማሳደግ ከደንበኞች ጋር ያለውን የረጅም ጊዜ አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው በተጨማሪም ሮሜል በቀጣይ ከሀገር ውስጥ አቅርቦት በተጨማሪም ወደ ውጪ ገበያም ለማቅረብ በሰፊው እየሰራ እንደሚገኝ ” ገልፀዋል ።

በዕለቱ የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ፣ የደህንነትና የጥራት መመዘኛዎችን ያሟሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን አስተዋውቀዋል። በገበያው ላይ ይፋ ከተደረጉት ዘመናዊ ምርቶች መካከል፦ የሮሜል ፒያኖ ሲሪየስ ስዊቾች (Piano Series Switches) እና ሶኬቶች (Sockets)፣ የሮሜል ብሬከሮች (Breakers)፣ የሮሜል ማግኔቲክ ትራክ ላይቶች (Magnetic Track Lights)፣ የሮሜል ሊኒየር ላይቶች (Linear Lights) ፤ የሮሜል ኬብል ትራንኪንግ (cable trunking) ፤ የሮሜል ዋተር ፕሩፍ ሲሊንግ ላይት (waterproof ceiling light) እና የሮሜል ዲስትሪቢዩሽን ቦርዶችን (Distribution Boards) በይፋ አስተዋውቀዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙ እንግዶች በዋና መሥሪያ ቤቱ የሚገኙ ዘመናዊ ሾውሩሞችን የጎበኙ ሲሆን፣ በሀገር ውስጥ የሚመረቱትን የኤሌክትሪክ ውጤቶች እንዲሁም ከውጭ የሚገቡትን ዘመናዊና ቅንጡ መብራቶች ጎብኝተዋል ።
ሮሜል ኤሌክትሪካል ለጥራት ያልተቆጠበ ትኩረት በመስጠትና ከደንበኞቹ ጋር የፈጠረውን የጋራ መተማመን በማጠናከር፣ በሀገሪቱ ያለውን የኤሌክትሪክ ምርቶች ለማዘመንና በጥራትም ከፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጧል። ድርጅቱ ይህንን የአጋርነት መድረክ ባህል በማድረግ በየዓመቱ መሰል መርሀግብሮችን እንደሚያዘጋጅም አስታውቋል።
ሮሜል ኤሌክትሪካል በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች አምራችና አቅራቢ ድርጅት ሲሆን፣ ከ20 ዓመታት በላይ ለኢንዱስትሪ፣ ለንግድና ለመኖሪያ ቤቶች የሚሆኑ ጥራታቸው የተረጋገጡ የኤሌክትሪክ ምርቶችን በማቅረብ በገበያው ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ስም ነው።

Address

Ghana Street
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30
Saturday 08:30 - 00:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ROMEL Electrical Equipment posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category