Murad

Call Directions Contact the business

Murad Abdii boruu

19/10/2022

የጭካኔ ጥግ ማብቂያው መቼ ነው?

በህፃን አቡበክር አብደላ ላይ የተፈፀመው ለመስማት አይደለም ለማሰብ እንኳን የሚዘገንን የወንጀል ድርጊት እጅጉኑ ረብሾኛል::

የአፋልጉን ማስታወቂያ ተለጥፎ ቀናት ሳያልፉ ወላጆች የልጃቸውን አካል ተቆራቆርጦ በማዳበሪያ ቤታቸው ላይ ተጥሎ ማግኘታቸውን መስማት ልብ ያሳምማል::

ይህን ዜና ከሰማውበት ደቂቃ ጀምሮ እጅግ እየረበሸኝ ይገኛል:: ልጆቼን በተመለከትኩኝ ቁጥር የህፃን አቡበክርን የጭካኔ ግድያ እየታወሰኝ ሰላም እየነሳኝ ነው:: እኛ ይህን ያህል ህመሙ ከተሰማን የወለደ አንጀት ፣ የአብራካቸው ክፋይን በዚህ መልኩ ያጡ ወላጆችን ስሜት ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል መገመት ይከብዳል::

ምን ያህል ከሰብዓዊነት ብናፈነግጥ ይሆን አይደለም ልንገድላቸው ይቅርና ለማየት የሚያሳሱንን ህፃናት ላይ እጃችንን ማንሳት ያስቻለን!?

በየጊዜው የህፃናት እገታ፣ ግድያ፣ እና የአስገድዶ መድፈር ወንጀልን በሚዲያ ብቻ ተዘግቦ እየቀረ እንድንላመደው እየተደረገ ይመስላል:

ወንጀለኞች ተይዘው ተገቢውን ቅጣት አገኙ የሚለውን የፍትህ ዜና ሳንሰማ ሌላ ተመሳሳይ ድርጊት መፈፀሙን እንሰማለን:: ሀገሪቱ ላይ ያለው የህግ ስርዓት ይህን መሰል ሰይጣናዊ ድርጊት በሚፈፅሙ ላይ የማያዳግም እና መቀጣጫ የሚሆን የቅጣት ብይን የማያስተላልፍ በመሆኑ ወንጀለኞችን ከጥፋታቸው ከማቀብ ይልቅ የልብ ልብ የሰጣቸው ይመስላል::

ህፃናት በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የነገ ህይወታቸው እንዲጨልም እየተደረገ ወንጀለኛው ግን ታስሮ የሚቀለብበት፣ ህፃናትን በግፍ ገድሎ እና አካል አጉድሎ፣ የነገን ሀገር ተረካቢዎች በአጭር እንዲቀጩ ያደረገን ወንጀለኛ በነፃነት ህይወቱን እንዲመራ መፍቀድ የወንጀሉ ተባባሪ ከመሆን አልያ ወንጀሉን ከማስቆም ይልቅ የማበረታት ያህል ነው::

ህይወትን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ለሚያጠፉ አረመኔዎች ተገቢው መቀጣጫ ሞት እንጂ ሌላ ሊሆን አይገባም::

ሞትን የደፈረ ሞት ብቻ ነው ሊያቆመው የሚችለው!!!

ዛሬ ላይ በሌሎች ህፃናት ላይ ደርሶ የሰማነው ጥቃት እንዲሁም በሌሎች ወላጆች ላይ የደረሰው ሀዘን እና ስብራት ነገ በኛም ቤት ላይ ላለመድረሱ ዋስትና የለንም::
መንግስት ህግ እንዲከበር እና ህግ እንዲፈራ ማድረግ ካልቻለ ወንጀልን መዳፈር እየቀለለ ጥፋት በምድሪቱ ላይ መስፋፋቱ አይቀሬ ነው::

Horaa bulaa Cidha jaalalaaKan gammachuuİsiniif haata'u
18/10/2022

Horaa bulaa
Cidha jaalalaa
Kan gammachuu
İsiniif haata'u

Ni darba  hunduu guyyaa isaa eeggata malee™
23/07/2022

Ni darba hunduu guyyaa isaa eeggata malee™

Halkan dheerateef bari'uun hin oolu!!
16/07/2022

Halkan dheerateef
bari'uun hin oolu!!

10/07/2022
10/07/2022

An Ethiopian Munshid (Islamic vocalist), social influencer, youth leader, trainer and economist.

09/07/2022

Alahamdulillah galanni keetuma yes Rabbi kan asiin nu geeyse
Eid mubarak all muslim

Address


Opening Hours

Monday 06:00 - 12:00
Wednesday 01:30 - 06:30
Saturday 12:00 - 06:00
Sunday 03:00 - 09:00

Telephone

+251929174653

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Murad posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Murad:

Shortcuts

  • Want your business to be the top-listed interior service?

Share